መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 41

1 ፤ እነሆ፥ ተስፋው ከንቱ ነው፤ያየው ሁሉ ስንኳ በፊቱ ይዋረዳል።
2 ፤ ያንቀሳቅሰውም ዘንድ የሚደፍር የለም፤እንግዲህ በፊቴ መቆም የሚችል ማን ነው?
3 ፤ እመልስለትስ ዘንድ መጀመሪያ የሰጠኝ ማን ነው?ከሰማይ ሁሉ በታች ያለው ገንዘቤ ነው።
4 ፤ ስለ አካላቱና ስለ ብርቱ ኃይሉ፥ስለ መልካም ሰውነቱ ዝም አልልም።
5 ፤ የውጪ ልብሱን ማን ይገፋል?በጥንድ መንጋጋውስ ውስጥ ማን ይገባል?
6 ፤ የፊቱንስ ደጆች የሚከፍት ማን ነው?በጥርሶቹ ዙሪያ ግርማ አለ።
7 ፤ ቅርፊቶቹ ጠንካራ ስለ ሆኑ እርሱ ትዕቢተኛ ነው፤በጠባብ ማተሚያ እንደ ታተሙ ናቸው።
8 ፤ እርስ በርሳቸው የተቀራረቡ ናቸውናነፋስ በመካከላቸው መግባት አይችልም።
9 ፤ እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው፤እስከማይለያዩም ድረስ ተያይዘዋል።
10 ፤ እንጥሽታው ብልጭታ ያወጣል፥ዓይኖቹም እንደ ወገግታ ናቸው።
11 ፤ ከአፉ ፋናዎች ይወጣሉ፥የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል።
12 ፤ እንደ ፈላ ድስትና እንደሚቃጠል ሸምበቆከአንፍንጫው ጢስ ይወጣል።
13 ፤ እስትንፋሱ ከሰልን ታቃጥላለች፥ነበልባልም ከአፉ ይወጣል።
14 ፤ በአንገቱ ኃይል ታድራለች፤ግርማ በፊቱ ይዘፍናል።
15 ፤ የሥጋውም ቅርፊት የተጣበቀ ነው፤እስከማይንቀሳቀሱም ድረስ በእርሱ ላይ ጸንተዋል።
16 ፤ ልቡ እንደ ድንጋይ የደነደነ ነው፤እንደ ወፍጮ ድንጋይ የጸና ነው።
17 ፤ በተነሣ ጊዜ ኃያላን ይፈራሉ፤ከድንጋጤም የተነሣ ያብዳሉ።
18 ፤ ሰይፍና ጦር፥ ፍላጻና መውጊያም ቢያገኙት አያሸንፉትም።
19 ፤ ብረትን እንደ ገለባ፥ናስንም እንደ ነቀዘ እንጨት ይቈጥራቸዋል።
20 ፤ ፍላጻ ሊያባርረው አይችልም፤የወንጭፍም ድንጋዮች እንደ ገለባ ይሆኑለታል።
21 ፤ በሎታውን እንደ ገለባ ይቈጥረዋል፤ሰላጢኑም ሲሰበቅ ይስቃል።
22 ፤ ታቹ እንደ ስለታም ገል ነው፤እንደ መዳመጫም በጭቃ ላይ ያልፋል።
23 ፤ ቀላዩን እንደ ድስት ያፈላዋል፤ባሕሩንም እንደ ሽቱ ምንቸት ያደርገዋል።
24 ፤ በስተ ኋላው ብሩህ መንገድን ያበራል፤ቀላዩም ሽበት ይመስላል።
25 ፤ ያለ ፍርሃት የተፈጠረ፥እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ የለም።
26 ፤ ከፍ ያለውን ሁሉ ይመለከታል፤በትዕቢተኞችም ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።