መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 20

1 ፤ ናዕማታዊውም ሶፋር መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ ስለዚህ በውስጤ ስላለው ችኰላ አሳቤ ትመልስልኛለች።
3 ፤ የሚያሳፍረኝንም ተግሣጽ ሰምቻለሁ፥የማስተዋሌም መንፈስ ይመልስልኛል።
4 ፤ ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ፥ ከዱሮ ዘመን ጀምሮ፥
5 ፤ የኃጢአተኛ ፉከራ አጭር መሆኑንየዝንጉዎችም ደስታ ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን?
6 ፤ ከፍታው ወደ ሰማይ ቢወጣ፥ራሱም እስከ ደመና ቢደርስ፥
7 ፤ እንደ ፋንድያ ለዘላለም ይጠፋል፤ያዩትም። ወዴት ነው? ይላሉ።
8 ፤ እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፤እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል።
9 ፤ ያየችውም ዓይን ዳግመኛ አታየውም፤ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከተውም።
10 ፤ ልጆቹ ድሆቹን ያቈላምጣሉ፤እጁ ሀብቱን ይመልሳል።
11 ፤ አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፤ነገር ግን ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል።
12 ፤ ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥ከምላሱም በታች ቢሰውረው፥
13 ፤ ቢጠብቀውም ባይተወውም፥በጕሮሮውም ቢይዘው፥
14 ፤ መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፤እንደ እፉኝትም ሐሞት በውስጡ ይሆናል።
15 ፤ የዋጠውን ሀብት ይተፋዋል፤እግዚአብሔርም ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል።
16 ፤ የእፉኝትን መርዝ ይጠባል፤የእባብም ምላስ ይገድለዋል።
17 ፤ የማሩንና የቅቤውን ፈሳሽወንዞቹንም አይመለከትም።
18 ፤ የድካሙን ፍሬ ሳይውጠው ይመልሰዋል፤እንደ ንግዱም ትርፍ አይደሰትም።
19 ፤ ድሀውን አስጨንቆአል፥ ትቶታልም፤ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአል።
20 ፤ ሆዱ ዕረፍትን አላወቀምናየወደደው ነገር አላዳነውም።
21 ፤ እርሱ ከበላ በኋላ ምንም አልተረፈም፤ስለዚህ በረከቱ አይከናወንለትም።
22 ፤ በጠገበ ጊዜ ይጨነቃል፤የችግረኞችም ሁሉ እጅ ታገኘዋለች።
23 ፤ ሆዱን ሳያጠግብእግዚአብሔር የቍጣውን ትኵሳት ይሰድድበታል፥ሲበላም ያዘንብበታል።
24 ፤ ከብረት መሣርያም ይሸሻል፥የናስም ቀስት ይወጋዋል።
25 ፤ እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፤ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፤ፍርሃትም ይወድቅበታል።
26 ፤ ጨለማ ሁሉ ስለ ከበረው ዕቃ ተዘጋጅቶአል፤በሰው አፍ እፍ የማትባል እሳት ትበላዋለች፤በድንኳኑ ውስጥ የቀረው ይጨነቅባታል።
27 ፤ ሰማይ ኃጢአቱን ይገልጥበታል፥ምድርም ትነሣበታለች።
28 ፤ የቤቱም ባለጠግነት ይሄዳል፤በቍጣው ቀን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያልፋል።
29 ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ከእግዚአብሔርም የተመደበ ርስቱ ይህ ነው።