መዝሙረ ዳዊት. Chapter 117

1 ሃሌ ሉያ።1 አሕዛብ ሁላችሁ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፥ ወገኖችም ሁሉ ያመስግኑት፤
2 ምሕረቱ በእኛ ላይ ጸንታለችና፤ የእግዚአብሔርም እውነት ለዘላለም ትኖራለች። ሃሌ ሉያ።